am_tn/psa/089/019.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው፣ አንባቢው እንዴት ዳዊት የተመረጠው ንጉሥ እንደሆነ ታሪኩን እንደሚያውቅ ይገምታል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ሀያል በሆነው ላይ ዘውድ አደርጌያለሁ/ጭኛለሁ

በአንድ ሰው ራስ ላይ ዘውድ መጫን ሰውየውን ንጉሥ የማድረግ ምልክት ነው፡፡ "ታላቁን ሰው አነግሰዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በቅዱሱ ቅባቴ እርሱን ቀባሁት

እዚህ ስፍራ በአንድ ሰው ራስ ላይ ዘይት ማፍሰስ እግዝአብሔር ያንን ሰው ንጉሥ እንዲሆን መሾሙን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

የእኔ እጅ እርሱን ይደግፈዋል፣ ክንዴም ያበረታዋል

እዚህ ስፍራ "እጅ" እና "ክንድ" የሚሉት ሁለቱም የያህዌ ሀይል እና ቁጥጥር ማለት ነው፡፡ "እኔ እደግፈዋለሁ ደግሞም አበረታዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የክፋት ወንድ ልጅ

ጸሐፊው የክፋት ተፈጥሮ ወይም ባህሪይ ያላቸውን "የክፋት ወንዶች ልጆች" በማለት ይገልጻቸዋል፡፡ "ክፉ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)