# አጠቃላይ መረጃ፡ ጸሐፊው፣ አንባቢው እንዴት ዳዊት የተመረጠው ንጉሥ እንደሆነ ታሪኩን እንደሚያውቅ ይገምታል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) # እኔ ሀያል በሆነው ላይ ዘውድ አደርጌያለሁ/ጭኛለሁ በአንድ ሰው ራስ ላይ ዘውድ መጫን ሰውየውን ንጉሥ የማድረግ ምልክት ነው፡፡ "ታላቁን ሰው አነግሰዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) # በቅዱሱ ቅባቴ እርሱን ቀባሁት እዚህ ስፍራ በአንድ ሰው ራስ ላይ ዘይት ማፍሰስ እግዝአብሔር ያንን ሰው ንጉሥ እንዲሆን መሾሙን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ) # የእኔ እጅ እርሱን ይደግፈዋል፣ ክንዴም ያበረታዋል እዚህ ስፍራ "እጅ" እና "ክንድ" የሚሉት ሁለቱም የያህዌ ሀይል እና ቁጥጥር ማለት ነው፡፡ "እኔ እደግፈዋለሁ ደግሞም አበረታዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ) # የክፋት ወንድ ልጅ ጸሐፊው የክፋት ተፈጥሮ ወይም ባህሪይ ያላቸውን "የክፋት ወንዶች ልጆች" በማለት ይገልጻቸዋል፡፡ "ክፉ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)