am_tn/psa/053/006.md

20 lines
1.4 KiB
Markdown

# ምነው የእስራኤል ድነት በመጣ!
እዚህ ጋ “ምነው” የሚለው ቃል ተስፋን ወይም ጸሎትን የሚገልጽ ቃለ አጋኖን ያስተዋውቃል። አ.ት፡ “የእስራኤል ድነት እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ወይም “ድነት እንዲመጣ እጸልያለሁ” (ቃለ አጋኖ የሚለውን ተመልከት)
# የእስራኤል ድነት ከጽዮን ይመጣል
ድነት መቅደሱ በጽዮን የሆነውን፣ አዳኙን እግዚአብሔርን ይወክላል። አ.ት፡ “የእስራኤል አዳኝ ከጽዮን ይመጣል” ወይም “እግዚአብሔር ከጽዮን ይመጣና እስራኤልን ያድናል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምርኮ በሚመልስበት ጊዜ
“እግዚአብሔር የተማረከ ሕዝቡን በሚያድንበት ጊዜ”
# ያዕቆብ ደስ ይለዋል፣ እስራኤልም ሐሴትን ያደርጋል
እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው። (See: Parallelism)
# ያዕቆብ
እዚህ ጋ “ያዕቆብ” የሚያመለክተው የያዕቆብ ዘር የሆኑትን እስራኤላውያንን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)