# ምነው የእስራኤል ድነት በመጣ! እዚህ ጋ “ምነው” የሚለው ቃል ተስፋን ወይም ጸሎትን የሚገልጽ ቃለ አጋኖን ያስተዋውቃል። አ.ት፡ “የእስራኤል ድነት እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ወይም “ድነት እንዲመጣ እጸልያለሁ” (ቃለ አጋኖ የሚለውን ተመልከት) # የእስራኤል ድነት ከጽዮን ይመጣል ድነት መቅደሱ በጽዮን የሆነውን፣ አዳኙን እግዚአብሔርን ይወክላል። አ.ት፡ “የእስራኤል አዳኝ ከጽዮን ይመጣል” ወይም “እግዚአብሔር ከጽዮን ይመጣና እስራኤልን ያድናል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምርኮ በሚመልስበት ጊዜ “እግዚአብሔር የተማረከ ሕዝቡን በሚያድንበት ጊዜ” # ያዕቆብ ደስ ይለዋል፣ እስራኤልም ሐሴትን ያደርጋል እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው። (See: Parallelism) # ያዕቆብ እዚህ ጋ “ያዕቆብ” የሚያመለክተው የያዕቆብ ዘር የሆኑትን እስራኤላውያንን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)