1.2 KiB
1.2 KiB
ብርቱ ሰራዊቱና ታላቅ አጀቡ
የእነዚህ ሁለት ሐረጎች መሠረታዊ ትርጉም አንድ ሲሆን የፈርዖን ሰራዊት ምን ያህል ብዙና ጠንካራ እንደ ሆነ አጽንዖት ይሰጣል።
እርሱን አይረዳውም
እዚህ ጋ “እርሱን” የሚለው ቃል የይሁዳን ንጉሥ ያመለክታል።
ቅጥሩን መመሸግ
ይህ የሚያመለክተው መሰላሎች ያሉትን ግምብ ሲሆን ግምቡ ላይ በማስደገፍ ወታደሮች በእርሱ ላይ በመውጣት ወደ ከተማይቱ ለመግባት ያስችላቸዋል።
የብዙዎችን ሕይወት ለመቁረጥ
“ብዙ ሰዎችን ለመግደል”
እነሆ፣ እጁን ዘረጋ
“ከዚያ እንኳን የከፋውን ነገር አደረገ፤ እጁን ዘረጋ”
ቃል ኪዳን ለማድረግ እጆቹን ዘረጋ
ይህ የሚያመለክተው የወዳጅነትና የስምምነት ምልክት እንዲሆን የሌላውን ሰው እጅ መያዝን ነው። እዚህ ጋ ቃሉ የሚወክለው ከባቢሎን ንጉሥ ጋር ያደረገውን የቃል ኪዳን መሐላ ነው። (See: Symbolic Action)