am_tn/psa/069/016.md

1.1 KiB

የኪዳንህ ታማኝነት መልካም ነው

“ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅፅል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ለኪዳንህ መልካምና ታማኝ ነህ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ ያለህ ምህረት ብዙ ነው

“አንተ ለእኔ በጣም መሀሪ ነህ”

ወደ እኔ ተመለስ

ወደ አንድ ሰው የመመለስ ሀሳብ ለእነርሱ ተገቢ ትኩረት መስጠት ወይም እነርሱን መርዳት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርዳኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከባሪያህ ፊትህን አትሰውር

የአንድ ሰው ፊት መሰወር ሌላ ሰውን ለመስማት ወይም ለመርዳት ፈቃደኛ አለመሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እባክህ ባሪያህን እርዳ” ወይም “እባክህ እርዳኝ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ጭንቅ ውስጥ

“በታላቅ መከራ ውስጥ”