# የኪዳንህ ታማኝነት መልካም ነው “ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅፅል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ለኪዳንህ መልካምና ታማኝ ነህ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) # ለእኔ ያለህ ምህረት ብዙ ነው “አንተ ለእኔ በጣም መሀሪ ነህ” # ወደ እኔ ተመለስ ወደ አንድ ሰው የመመለስ ሀሳብ ለእነርሱ ተገቢ ትኩረት መስጠት ወይም እነርሱን መርዳት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርዳኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ከባሪያህ ፊትህን አትሰውር የአንድ ሰው ፊት መሰወር ሌላ ሰውን ለመስማት ወይም ለመርዳት ፈቃደኛ አለመሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እባክህ ባሪያህን እርዳ” ወይም “እባክህ እርዳኝ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ) # ጭንቅ ውስጥ “በታላቅ መከራ ውስጥ”