2.1 KiB
2.1 KiB
ሸክማችንን በየእለቱ ይሸከማል
“የእኛን ከባድ ሸክም በየቀኑ ይሸከማል፡፡” ጌታ ለህዝቡ የሚያደርገው እንክብካቤ እርሱ በአካል ችግሮቻቸውን እንደ ሸክም እንደሚሸከም ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ደህንነታችን የሆነው እግዚአብሔር… አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው
እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እዚህ ላይ “ደህንነታችን” የሚለው “አዳነ” በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያድን አምላክ… አምላካችን እኛን የሚያድነን አምላክ ነው፡፡” (ትይዩነት እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
የጠላቶቹን ራስ ይቀጠቅጣል
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ለመግደል ዓላማ በማድረግ የእነርሱን ራስ በመቀጥቀጥ የሚገድል ጦረኛ ተዋጊ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳቸውን በመፈንከት ጠላቶቹን ይገድላል” (ተለዋጭ ዘይቤ አና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ፀጉራም አናት
በጦርነት ጊዜ ወታደሮች ፀጉራቸውን አለመቆረጣቸው የሚዘወተር ልማድ የነበረ ይመስላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ረጅም ፀጉር ያለው አናት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
በእርሱ ላይ በሀጢአት የሚሄዱትን
እግዚአብሔርን ማሳዘን በሀጢአት መካከል መሄድ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተለምዶ በእርሱ ላይ ሀጢአት ያደርጋሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)