# ሸክማችንን በየእለቱ ይሸከማል “የእኛን ከባድ ሸክም በየቀኑ ይሸከማል፡፡” ጌታ ለህዝቡ የሚያደርገው እንክብካቤ እርሱ በአካል ችግሮቻቸውን እንደ ሸክም እንደሚሸከም ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ደህንነታችን የሆነው እግዚአብሔር… አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እዚህ ላይ “ደህንነታችን” የሚለው “አዳነ” በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያድን አምላክ… አምላካችን እኛን የሚያድነን አምላክ ነው፡፡” (ትይዩነት እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) # የጠላቶቹን ራስ ይቀጠቅጣል እግዚአብሔር ጠላቶቹን ለመግደል ዓላማ በማድረግ የእነርሱን ራስ በመቀጥቀጥ የሚገድል ጦረኛ ተዋጊ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳቸውን በመፈንከት ጠላቶቹን ይገድላል” (ተለዋጭ ዘይቤ አና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) # ፀጉራም አናት በጦርነት ጊዜ ወታደሮች ፀጉራቸውን አለመቆረጣቸው የሚዘወተር ልማድ የነበረ ይመስላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ረጅም ፀጉር ያለው አናት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) # በእርሱ ላይ በሀጢአት የሚሄዱትን እግዚአብሔርን ማሳዘን በሀጢአት መካከል መሄድ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተለምዶ በእርሱ ላይ ሀጢአት ያደርጋሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)