am_tn/isa/33/10.md

28 lines
2.8 KiB
Markdown

# እነሣለሁ
መነሣት ወይም መቆም ከእንግዲህ ወዲያ ማየትና ማሰብ እንደማይኖርና በዚያ ፈንታ የሥራ መጀመሪያ እንደሆነ የሚያሳይ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "መሥራት እጀምራለሁ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# አሁን ወደ ላይ ከፍ እላለሁ፣ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ እነዘህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በእግዚአብሔር መክበር ላይ አጽንዖት ያደርጋሉ፡፡ አት፡- "አሁን እኔ ራሴን አከብራለሁ፣ ሁሉ ሊያከብረኝ የሚገባኝ እንደሆነም አሳያለሁ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ እና አጓዳኝነት ተመልከት)
# ገለባን ትፀንሳላቸሁ፣ እብቅንም ትወልዳላችሁ
ይህ የአሦራውያን ማቀድ እናት ልጅን እንደምትወልድ እቅዶቻቸውን እንደሚፀንሱና እንደሚወልዱ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ እቅዶቻቸውን ከገላባ ጋር እያስተያየ ከንቱ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ አት፡- "እንደ ገለባና ሳር ከንቱ የሆኑ እቅዶችን ታቅዳላችሁ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# ተቆርጦ እንደ ቀረ ደረቅ የእህል ግንድ
ፍሬ የሚሸከመው ክፍል ከተቆረጠ በኋላ በምድር ላይ የተተው ደረቅ የተክል ክፍል፡፡
# እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት
በዚህ ስፍራ የአሦራውያን እቅዶች እንደ እስትንፋሳቸው ተጥቀስዋል፡፡ ይህ እቅዶቻቸው በተጨባጭ ሰውነታቸውን እንደሚያቃጥል አድርጎ እቅዶቻቸው ለሞት እንደሚዳርጓቸው ይናገራል፡፡ አት፡- "እቅዶቻችሁ ይገድሉአችኋል' (ምትክ ስምና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፣ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ
ይህ የአሕዛብ አስከሬን የሚቃጠልበትን መንገድ እሾህ ከሚቃጠልበት መንገድ ጋር ያስተያያል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽም ሊገለጽም ይችላል፡፡ አት፡- "ገበሬ እሾህን እንደሚቆርጥና እንደሚያቃጥል እሳት የአሕዛብን አስከሬን ለኖራ ያቃጥላል፡፡' (ዘይቤአዊ ንግግርና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
# ኖራ
የተቃጠሉ አጥንቶች አመድ