2.8 KiB
እነሣለሁ
መነሣት ወይም መቆም ከእንግዲህ ወዲያ ማየትና ማሰብ እንደማይኖርና በዚያ ፈንታ የሥራ መጀመሪያ እንደሆነ የሚያሳይ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "መሥራት እጀምራለሁ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
አሁን ወደ ላይ ከፍ እላለሁ፣ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ እነዘህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በእግዚአብሔር መክበር ላይ አጽንዖት ያደርጋሉ፡፡ አት፡- "አሁን እኔ ራሴን አከብራለሁ፣ ሁሉ ሊያከብረኝ የሚገባኝ እንደሆነም አሳያለሁ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ እና አጓዳኝነት ተመልከት)
ገለባን ትፀንሳላቸሁ፣ እብቅንም ትወልዳላችሁ
ይህ የአሦራውያን ማቀድ እናት ልጅን እንደምትወልድ እቅዶቻቸውን እንደሚፀንሱና እንደሚወልዱ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ እቅዶቻቸውን ከገላባ ጋር እያስተያየ ከንቱ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ አት፡- "እንደ ገለባና ሳር ከንቱ የሆኑ እቅዶችን ታቅዳላችሁ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
ተቆርጦ እንደ ቀረ ደረቅ የእህል ግንድ
ፍሬ የሚሸከመው ክፍል ከተቆረጠ በኋላ በምድር ላይ የተተው ደረቅ የተክል ክፍል፡፡
እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት
በዚህ ስፍራ የአሦራውያን እቅዶች እንደ እስትንፋሳቸው ተጥቀስዋል፡፡ ይህ እቅዶቻቸው በተጨባጭ ሰውነታቸውን እንደሚያቃጥል አድርጎ እቅዶቻቸው ለሞት እንደሚዳርጓቸው ይናገራል፡፡ አት፡- "እቅዶቻችሁ ይገድሉአችኋል' (ምትክ ስምና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፣ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ
ይህ የአሕዛብ አስከሬን የሚቃጠልበትን መንገድ እሾህ ከሚቃጠልበት መንገድ ጋር ያስተያያል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽም ሊገለጽም ይችላል፡፡ አት፡- "ገበሬ እሾህን እንደሚቆርጥና እንደሚያቃጥል እሳት የአሕዛብን አስከሬን ለኖራ ያቃጥላል፡፡' (ዘይቤአዊ ንግግርና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ኖራ
የተቃጠሉ አጥንቶች አመድ