am_tn/ezk/17/07.md

1.2 KiB

ሌላ ታላቅ ንስር

“ሌላ ግዙፍ ንስር”

እነሆ

እዚህ ጋ፣ “እነሆ” የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው አስገራሚ መረጃ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል።

ይህ የወይን ተክል ሥሮቹን ወደ ንስሩ መለሰ

እግዚአብሔር የሚናገረው እንደ ሰው ማድረግ ይችል ይመስል አስፈላጊውን ምግብ ከእርሱ ያገኝ ዘንድ ሥሮቹን ሆን ብሎ ወደ ሌላኛው ንስር ስለሚያዞረው ስለ ወይን ተክል ነው። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ውሃ ያጠጡት ዘንድ ተተክሎ ከነበረበት ስፍራ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ውሃ ያገኝ ዘንድ የመጀመሪያው ንስር ተክሎ ከነበረበት ስፍራ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ተተክሎ ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የወይኑን ተክል የመጀመሪያው ንስር ተክሎት ነበር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)