am_tn/num/32/06.md

1.5 KiB

ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ እዚህ ትቀመጣላችሁን?

ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ሮቤልንና ጋድን ለመገሰፅ ብሎ ነው፡፡“ወንድሞቸችሁ ጦርነት ላይ እያሉ እናንተ በዚህ ምድር መቀመጣችሁ ተገቢ አይደለም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር የሰጣቸውን …..የሰውን ልብ ለምን ታደክማላችሁ?

ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ከሮቤልና ከጋድ ሃሣብ ሕዝቡን ለመከላከል ነው፡፡“እግዚአብሔር የሰጣቸውን ….. የሰውን ልብ አታድክሙ”ወይም “ድርጊታችሁ የሰዎችን ልብ ሊያደክሙ ይችላሉ….እግዚአብሔር የሰጣቸውን”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የእሥራኤልን ሕዝብ ልብ ከመሄድ ታደክሙታላችሁ

እዚህ ላይ“ልብ”የሚለው ቃል የሚወክለው ራሣቸው ሰዎቹን ሲሆን የሚያመለክተውም የስሜታቸው መሠረት የሆነውን ነገርነው፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ እንዳይሄድ ተስፋ ታስቆርጡታላችሁ”ወይም “የእሥራኤል ሕዝብ እንዳይሄድ ምክኒያት ትሆናላችሁ”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)