am_tn/isa/05/03.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ወይኑ እርሻ በተናገረው ምሳሌ እግዚአብሔርን የሚወክለው ባለቤት፣ የወይን እርሻውን በተመለከተ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ሰዎች ይናገራል፡፡

በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች

ይህ የሚናገረው በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነው፤ ስለዚህ በብዙ ቁጥር መናገር ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የምትኖሩ ሁሉ››

ኢየሩሳሌም… ይሁዳ

‹‹ይሁዳ›› የደቡባዊው እስራኤል መንግሥት ስም ነበር፤ ዋና ከተማውም ኢየሩሳሌም ነበር፡፡

በእኔና በወይን ቦታዬ መካከል እስቲ ፍረዱ

በሁለት ነገሮች መካከል ያለ ክፍት ቦታ ብዙውን ጊዜ ከሁለት አንዱን የመምረጥን ሐሳብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማን ትክክል እንደ ነበር ፍረዱ፤ እኔ ወይስ የወይን ቦታዬ››

ከዚህ ካደረግሁለት በላይ ለወይኔ ቦታ ምን ሊደረግለት ይገባ ነበር?

ባለቤቱ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ስለ ወይን ቦታው ጠንከር አድርጐ ለመናገር ነው፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለወይን ቦታዬ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አድርጌአለሁ››

መልካም የወይን ፍሬ ያፈራል ብዬ ስጠብቅ ለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?

ባለቤቱ ጥያቄውን ያቀረበው የወይን ቦታው መልካም ፍሬ ማፍራት እንደ ነበረበት ለመናገር ነው፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የፈለግሁት ጥሩ ፍሬ እንዲያፈራ ነበር፣ ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ››