24 lines
2.1 KiB
Markdown
24 lines
2.1 KiB
Markdown
|
# አጠቃላይ መረጃ
|
||
|
|
||
|
ኢሳይያስ ስለ ወይኑ እርሻ በተናገረው ምሳሌ እግዚአብሔርን የሚወክለው ባለቤት፣ የወይን እርሻውን በተመለከተ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ሰዎች ይናገራል፡፡
|
||
|
|
||
|
# በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች
|
||
|
|
||
|
ይህ የሚናገረው በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነው፤ ስለዚህ በብዙ ቁጥር መናገር ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የምትኖሩ ሁሉ››
|
||
|
|
||
|
# ኢየሩሳሌም… ይሁዳ
|
||
|
|
||
|
‹‹ይሁዳ›› የደቡባዊው እስራኤል መንግሥት ስም ነበር፤ ዋና ከተማውም ኢየሩሳሌም ነበር፡፡
|
||
|
|
||
|
# በእኔና በወይን ቦታዬ መካከል እስቲ ፍረዱ
|
||
|
|
||
|
በሁለት ነገሮች መካከል ያለ ክፍት ቦታ ብዙውን ጊዜ ከሁለት አንዱን የመምረጥን ሐሳብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማን ትክክል እንደ ነበር ፍረዱ፤ እኔ ወይስ የወይን ቦታዬ››
|
||
|
|
||
|
# ከዚህ ካደረግሁለት በላይ ለወይኔ ቦታ ምን ሊደረግለት ይገባ ነበር?
|
||
|
|
||
|
ባለቤቱ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ስለ ወይን ቦታው ጠንከር አድርጐ ለመናገር ነው፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለወይን ቦታዬ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አድርጌአለሁ››
|
||
|
|
||
|
# መልካም የወይን ፍሬ ያፈራል ብዬ ስጠብቅ ለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?
|
||
|
|
||
|
ባለቤቱ ጥያቄውን ያቀረበው የወይን ቦታው መልካም ፍሬ ማፍራት እንደ ነበረበት ለመናገር ነው፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የፈለግሁት ጥሩ ፍሬ እንዲያፈራ ነበር፣ ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ››
|