እግዚአብሔር የሥራውን ብርታት ለሕዝቡ ያሳያቸው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር የሥራውን ብርታት ለሕዝቡ ያሳያቸው የአሕዛብን ርስት ለእነርሱ በመስጠቱ ነው፡፡ [111፡6-7]
የእግዚአብሔር ትእዛዝ መከበር ያለበት እንዴት ነው?
ትእዛዛቱ ሁሉ በታማኝነትና በአግባቡ መከበር አለባቸው፡፡ [111፡8]
ጸሐፊው የእግዚአብሔርን ስም የገለጸው እንዴት ነው?
ጸሐፊው የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ፣ ‹‹ስሙ የተቀደሰና የተፈራ ነው፡፡›› ይላል፡፡ [111፡9]