am_2ch_text_ulb/18/01.txt

1 line
995 B
Plaintext
Raw Normal View History

\c 18 \v 1 ኢዮሣፍጥ ታላቅ ባለጠግነትና ክብር ነበረው፡፡ ከቤተሰቦቹ አንዱ ሴት ልጁን እንዲያገባ በማድረግ ከአክዓብ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡ \v 2 ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ፡፡ አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ በርካታ በጎችንና በሬዎችን አረደላቸው፡፡ ከእርሱም ጋር ሬማት ዘገለአድን ለማጥቃት ይሄድ ዘንድም አክዓብ አሳመነው፡፡ \v 3 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦ "ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለአድ ትሄዳለህን?" አለው፡፡ ኢዮሣፍጥም ፦"እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በጦርነቱ ውስጥ ካንተ ጋር አብረን እንሆናለን" ብሎ መለሰለት፡፡