2016-12-05 17:19:27 +00:00
|
|
|
\c 18 \v 1 ኢዮሣፍጥ ታላቅ ባለጠግነትና ክብር ነበረው፡፡ ከቤተሰቦቹ አንዱ ሴት ልጁን እንዲያገባ በማድረግ ከአክዓብ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡ \v 2 ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ፡፡ አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ በርካታ በጎችንና በሬዎችን አረደላቸው፡፡ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለአድን ለማጥቃት ይሄድ ዘንድም አክዓብ አሳመነው፡፡ \v 3 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦ "ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለአድ ትሄዳለህን?" አለው፡፡ ኢዮሣፍጥም ፦" እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በጦርነቱ ውስጥ ካንተ ጋር አብረን እንሆናለን" ብሎ መለሰለት፡፡
|