am_tn/psa/125/001.md

1.8 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ

ተመሳሳይነት በዕብራውያን ስነግጥም የተለመደ ነው

መዝሙረ መዐርግ

ሊሆን የሚችለው ትርጉም 1) “ለማክበር ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ የዘመሩት መዝሙር ነው፡፡” ወይም 2) “ወደ መቅደሱ ለመግባት ሕዝቡ የዘመሩት መዝሙር ነው” ወይም 3) “ቃላቶቹ እንደ እርምጃ የሆኑ መዝሙሮች ናቸው”፡፡ በመዝሙረ ዳዊት 120፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት

በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።

በእግዚአብሔር የታመኑ ሰዎች ልክ እነርሱ እንደ ማይነቀሳቀስ የፅዮን ተራራ እንደሆኑ መስሎ ይናገራል፡፡

ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ፣ ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው።

የእግዚአብሔር ጥበቃ ልክ እንደ እየሩሳሌምን እንደ ከበበ ተራራ መስሎ ይናገራል፡፡ ኢየሩሳሌም በብዙ ተራራዎች ተከበው ነበር ይህም ከጥቃት ጠብቋቸው ነበር፡፡ “ልክ ተራራ ኢየሩሳሌምን እንደከበባት እና እንደጠበቃት ሁሉ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይጠብቃል፡፡”

ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም

ይህ ሐረግ ሁልጊዜ እንደ ሆነ ያለክታል

የክፉዎች በትር

የክፉዎች በትር የመለው ሐረግ የሚያመለክተው የክፉ ሰዎችን ግዛትን ነው፡፡ “ክፉ ሰዎች” ወይም “ክፉ መሪዎች”