1.8 KiB
1.8 KiB
ውቅያኖሶች…የውቅያኖስ
አንዳንድ ቅጂዎች "ጎርፍ…የጎርፍ" ይላሉ፡፡ ቃሉ ብዙውን ጊዜ ወንዝን ያመለክታል (በመዝሙር 72፡8 ላይ "ወንዝ" የሚለውን ይመልከቱ) ፣ ነገር ግን እዚህ ስፍራ የተመረጠው "ውቅያኖሶች…የውቅያኖሶች" የሚለው እንጂ ወንዞች የሚለው አይደለም፤ ምክንያቱም "የሚላተም እና የሚያጎራ" "ማዕበል" ያለው ውቅያኖስ እንጂ ወንዝ አይደለም
የውቅያኖስ ማዕበል እና ማጎራት፣ ድምጻቸውን አነሱ
ዘማሪው ማዕበልን የሚገልጸው መናገር እንደሚችል ሰው አድርጎ ነው፡፡ "ማዕበላቸው ሲጋጭ እን ሲያጓራ ታላቅ ድምጽ አሰሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ማጓራት
ረጅም እና ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት
ከብዙ ማዕበል መጋጨት በላይ፣ የባህር ታላቅ ነውጥ
"የባህር ታላቅ ነውጥ" የሚለው ሀረግ "ብዙ ማዕበል" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖረው እነዚህ ማዕበሎች እንዴት ታላቅ እንደሆኑ ትኩረት ይሰጣል፡፡ "ከባህሩ ታላቅ ነውጦች ሁሉ በላይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትጉም የሚለውን ይመልከቱ)
ሞገድ
ከባህሩ ወደ ዳርቻ የሚመጣ ትልቅ ማዕበል
በላይ
ዘማሪው እግዚአብሔር የሚኖርበትን ከምድር በላይ ከፍ ብሎ እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል፡፡ "በሰማያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)