2.6 KiB
አጠቃላይ መረጃ፡-
ዳዊት እስራኤላውያን በምድረ በዳ የተጓዙት የጉዞ ታሪክ መናገር ቀጥሏል፡፡ በዚህ የታሪክ ክፍል ውስጥ እስራኤላውያን በጦርነት በጠላቶቻቸው ላይ ድል አድርገዋል፡፡
ትእዛዙን የሚያውጁት … ሰራዊት
እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን መልእክት ለሌሎች ተናገሩ፡፡ እነርሱ እጅግ ታላቅ ሰራዊት እንደ ነበሩ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ሀረጉ በሴት ፆታ ስለተገለፀ አንዳንድ ትርጉሞች “ትእዛዙን ያወጁት ሴቶች… ሰራዊት” ብለው ተርጉመውታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
የሰራዊቶች ንጉስ… ለምን ይህን ታደርጋለህ?
በ መዝሙረ ዳዊት 68:12-13 ያለው መረጃ ትርጉሙን የበለጠ በቀላሉ መረዳት እንዲቻል ለማድረግ ቅደም ተከተሉ ተስተካክሏል፡፡ (የጥቅስ ድልድዮች የሚለውን ይመልከቱ)
የሰራዊት ነገስታት ፈጥነው ይሸሻሉ፣ እነርሱ ይሸሻሉ
ነገስታቱ ራሳቸውንና ሰራዊታቸውን በሙሉ ይወክላሉ፡፡ እነርሱ የሸሹት በእስራኤል ሰራዊት በመሸነፋቸው ምክንያት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገስታቱና ሰራዊታቸው በሙሉ በመሸነፋቸው ምክንያት ከእኛ ሸሹ” (ወካይ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ምርኮ
ከተሸነፈው ሰራዊት የተወሰዱና ድል ወዳደረገው ሰራዊት ቤተ የተወሰዱ ነገሮች፡፡
በብር የተሸፈኑ ርግቦች… ወርቅ
የዚህ ትርጉም አንዳንድ ምርኮዎች በከበሩ ብረቶች የተሸፈኑ ስለሆኑ በጣም ውድ ናቸው ማለት ነው፡፡
እናንተ አንዳንድ ሰዎች በበጎች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ፣ ይህንን ለምን ታደርጋላችሁ?
ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው በጦርነት ውስጥ ያልተሳተፉትን ሰዎች ለመገሰፅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በበጎች በረት መካከል የቆዩት ሰዎች በዚያ ሊቆዩ አይገባቸውም ነበር፤ ወደ ጦርነቱ መሄድ ነበረባቸው” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)