am_tn/psa/068/004.md

2.6 KiB

ለስሙ

ይህ እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእርሱ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በደመናት ላይ የሚሄደውን

የእግዚአብሔር ህልውና በህዝብ መካከል እርሱ በፈረስ ወይም በሰረገላ ላይ ሆኖ ወደ ምድር እንደሚሄድ ሆኖ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አባት ለሌላቸው አባት ነው

እግዚአብሔር ለወላጅ አልባዎች እንደ አባት የሚሆን ሩህሩህ አምላክ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወላጆች ለሌላቸው ልጆች እንደ አባት የሚሆን አምላክ”” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለባልቴቶች ዳኛ

እግዚአብሔር ባልቴቶችን የሚጠብቅ ምህረት የተሞላ አምላክ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የባልቴቶች ጠባቂ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተሰብ መካከል ያኖራቸዋል

እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተሰብ መካከል እንደሚያኖራቸው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ “እግዚአብሔር ቤተሰብ ለሌላቸው ቤተሰብ ይሰጣቸዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ እስረኞችን ከታሰሩበት እየዘመሩ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል

እግዚአብሔር እስረኞችን ከታሰሩበት እንዲወጡ የሚመራቸው እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር እስረኞችን ነፃ ያወጣል፤ በደስታም እንዲዘምሩ ያደርጋቸዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አመፀኞች

ይህ የስም ቅፅል አመፀኛ ሰዎችን የሚያመለክተ ሲሆን በቅፅል ወይም በስም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አመፀኛ ሰዎች” ወይም” በእርሱ ላይ የሚያምፁ ሰዎች” (የስም ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ምድረ በዳ

እግዚአብሔር አመፀኞችን ስለ መቅጣቱ ሲናገር እርሱ እጅግ በጣም ሞቃት የሆነ ምድረ በዳ እንዲኖሩ እንዳስገደዳቸው ተደርጎ ተገልጧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም ሞቃት እና ደረቅ ምድር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)