1.5 KiB
1.5 KiB
ለሙዚቀኞቹ አለቃ
“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”
ለማሃላዝ የተዘጋጀ
ይህ ምናልባት አንድን የሙዚቃ ስልት ዓይነት ያመለክት ይሆናል። (ቃላትን ቅዳ ወይም ተዋስ የሚለውን ተመልከት)
ማሺል
ይህ ምናልባት አንድን የሙዚቃ ስልት ዓይነት ያመለክት ይሆናል። ይህንን በመዝሙር 32፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የሰው ልጆች
ይህ ሰዎችን ሁሉ ያመለክታል።
እርሱን የሚፈልግ
እግዚአብሔርን እንደ ሰው መፈለግ እርሱን እንደ “መፈለግ” ሆኖ ተነግሯል። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) እግዚአብሔርን ለማወቅ መፈለግ። አ.ት፡ “እርሱን ለማወቅ የሚፈልግ” ወይም 2) እግዚአብሔርን ማምለክ። አ.ት፡ “እርሱን የሚያመለክ” የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሁሉም ወደ ኋላ ተመልሰዋል
እግዚአብሔርንና ትክክል የሆነውን መተው ወደ ኋላ እንደ መመለስ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሁሉም ትክክል የሆነውን ከማድረግ ወደ ኋላ ተመልሰዋል” ወይም “ሁሉም እግዚአብሔርን ትተውታል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)