am_tn/psa/051/017.md

20 lines
1.6 KiB
Markdown

# የእግዚአብሔር መሥዋዕት
“እግዚአብሔርን የሚያስደስት መሥዋዕት”
# የተሰበረ መንፈስ
የተሰበረ መንፈስ ትሁት ጠባይን ይወክላል። አ.ት፡ “ትህትና” ወይም “ትሁት የሆነ ሰው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# የተሰበረና የተጸጸተ ልብ
ትሁት መሆንና ስለ ኃጢአት ማዘን የተሰበረና የተጸጸተ ልብ እንዳለው ሰው መሆን ተደርጎ ተነግሯል። ልብ ስሜትንና ፈቃድን ይወክላል። አ.ት፡ “ሀዘንና ትህትና” ወይም “ስለ ኃጢአቱ የሚያዝንና ትሁት የሆነ ሰው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# የኢየሩሳሌምን ግንቦች አድስ
የአንድ ከተማ ግንቦች ከተማይቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሰዎች ይጠብቃሉ። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “የኢየሩሳሌምን ግንቦች እንድናድስ አስችለን” ወይም 2) “ኢየሩሳሌምን ጠብቃትና አበርታት” የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# ሕዝባችን በመሰዊያህ ላይ ኮርማዎችን ያቀርባሉ
ኮርማ ወደ በሬነት እያደገ ያለ ነው። እግዚአብሔር በሰጠው መመሪያ መሠረት ኮርማዎች አብዛኛውን ጊዜ ለመሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች ናቸው።