am_tn/psa/051/010.md

1.3 KiB

በውስጤ ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ

እዚህ ጋ፣ “ልብ” ምኞትንና ስሜትን ይወክላል። ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ መሰጠትና መታዘዝ ንጹሕ ልብ እንዳለው ሰው ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሙሉ በሙሉ ለአንተ የተሰጠ ሰው አድርገኝ” ወይም “ሁልጊዜ አንተን ለመታዘዝ እንድፈልግ አድርገኝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ትክክለኛውን መንፈስ በውስጤ አድስ

እዚህ ጋ “መንፈስ” የሚወክለው የዳዊትን ጠባይና ምኞት ነው። አ.ት፡ “ጠባዬን ትክክለኛ አድርገው” ወይም “ሁልጊዜ ትክክል የሆነውን እንዳደርግ አድርገኝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከሀልዎትህ አታርቀኝ

“ከአንተ ተለይቼ እንድሄድ አታስገድደኝ”። በእግዚአብሔር የተተወ መሆን ከእርሱ ተለይቶ እንዲሄድ እንደመገደድ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከሕዝብህ እንደ አንዱ አትተወኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)