1.3 KiB
1.3 KiB
ነገር ግን ጠላቶቼ እጅግ ብዙ ናቸው … በጣም ብዙ ናቸው
እነዚህ ሁለትም ሐረጎች በመሠረቱ የሚናገሩት ተመሳሳይ ነገር ነው። (See: Parallelism)
መልካም ባደረግሁ ክፉ ይመልሱልኛል
የጸሐፊው ጠላቶች ድርጊት፣ እንደ ገንዘብ ግብይት፣ ባደረገው መልካም ነገሮች ምትክ ክፉ ነገሮችን እንደመለሱለት ተደርጎ ተነግሯል። የነገር ስም የሆነው “ክፉ” እና “መልካም” እንደ ቅጽል ሊነገሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “መልካም ከሆንኩላቸው በኋላ ክፉን ነገር ያደርጉብኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
ክሶችን ይወረውሩብኛል
የጸሐፊው ጠላቶች እርሱን የሚከሱበት መንገድ ክሶቹ ድንጋዮች የሆኑ ይመስል በእርሱ ላይ እንደወረወሩበት ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
መልካሙን ተከተልሁ
ጸሐፊው መልካምን ነገር መመኘቱ ከመልካም ነገሮች በስተኋላ እንደሮጠ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)