am_tn/psa/009/007.md

16 lines
1.2 KiB
Markdown

# ያህዌ ለዘላለም ይኖራል
“ይኖራል” የሚለው ቃል የሚወክለው በዙፋኑ እንደ ንጉሥ መኖርን ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ያህዌ ለዘላለም በዙፋኑ ይቀመጣል” ወይም “ያህዌ ለዘላለም ይገዛል” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)
# መንበሩንም ለፍርድ አፍንቶአል
“መንበሩ” የሚለው ቃል ዙፋኑን ወይም አገዛዙን ይወክላል። አማራጭ ፍቺ 1) “በሰዎች ለመፍረድ ይገዛል” ወይም “በጽድቅ በሰዎች ላይ ይገዛል” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)
# በዓለም በጽድቅ ይፈርዳል … በፍትህ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል
እነዚህ ሁለት ሃረጎች ተመሳሳይ ሃሳብ አላቸው (ትይዩነትን ይመልከቱ)
# በጽድቅ በዓለም ላይ ይፈርዳል
“ዓለም” የሚለው ቃል እዚህ ጋር የሚወክለው በዓለም ያሉትን ሰዎች ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “በጽድቅ በዓለም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)