am_tn/num/06/25.md

1.3 KiB

ፊቱን ያብራልህ

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ለሆነ ሰው በጎ አስተሳሰብ አለው ማለት ነው፡፡በፈገግታም ሊገለፅ ይችላል፡፡አሕፅሮት ስሙ በግሥ መልክ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ፈገግ ሲልልህ”ወይም“ወደ አንተ በቅንነት ሲመለከት”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በርህራሄ ይመልከትህ

እዚህ ላይ “ይመልከትህ”የሚለው ቃል በዚያ ሰው ላይ በጎ የሆነ አስተያያት እንዳለው የሚገልፅ ነው፡፡“አደላልህ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ …ሰላምንም ይስጥህ

እዚህ ላይ “አንተ”የሚለው ቃል ነጠላ ነው፡፡(አንተ በሚል በተለያዩ መልኮች የተገለፁትን ይመልከቱ)

ስሜን መሥጠት ይኖርባቸዋል

እዚህ ላይ እግዚአብሔር “ስሜን”ሰጥቻለሁ ብሎ በመናገሩ እሥራኤላውያን የራሱ እንደሆኑ ያውጃል፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ የእኔ መሆናቸውን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)