am_tn/isa/43/25.md

28 lines
1.5 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ
ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡
# እኔ፣ እኔው ነኝ
‹‹እኔ›› የሚለው ቃል የተደገመው አጽንዎት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ብቻ ነኝ››
# በደልህን የምደመስስ
ኀጢአትን ይቅር ማለት፣ 1) መደምሰስና መጥረግ እንደሆነ፣ ወይም 2) የተጻፈውን ኀጢአት መሰረዝ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንዳች ነገር እንደሚደመስስ ሰው ኀጢአትህን ይቅር የምል›› ወይም፣ ‹‹የተጻፈውን ኀጢአት እንደሚሰርዝ ሰው ኀጢአትህን ይቅር የምል››
# ስለ ራሴ ስል
‹‹ስለ ክብሬ›› ወይም፣ ‹‹ስለ ማንነቴ››
# አላስብም
‹‹አላስታውስም››
# ንጹሕ መሆንህን አስረዳ
ምንም እንኳ ያንን ማድረግ እንደማይችሉ ቢያውቅም፣ እነርሱ ላይ ከቀረበው ክስ ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ያህዌ ሕዝቡን ይጠይቃል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጹሕ መሆናችሁን ማረጋገጥ ከቻላችሁ ማስረጃ አቅርቡ››
# ንጹሕ እንድትሆኑ
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ንጹሕ መሆናችሁን ማስረዳት እንድትችሉ››