am_tn/isa/11/14.md

20 lines
1.1 KiB
Markdown

# በፍልስጥኤም ተራሮች ላይ ቁልቁል ይበርራሉ
የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ሰውን ወይም እንስሳን ለማጥቃት በድንገት ቁልቁል በሚበሩ ወፎች ተመስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እዚያ ያሉትን ሰዎች ለማጥቃት ወደ ፍልስጥኤም ተራሮች በፍጥነት ይሄዳሉ››
# የግብፅ ባሕረ ሰላጤ
‹‹ባሕረ ሰላጤ›› በከፊል በመሬት የተከበበ ትልቅ የውሃ አካል ነው፡፡
# በሚጋረፍ ነፋስ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ያንቀሳቅሳል
እጁን በአንዳች ነገር ላይ ማንቀሳቀሱ የመለወጥ ኀይሉን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በታላቅ ኀይሉ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ የሚጋረፍ ነፋስ ያነፍሳል››
# የሚጋረፍ ነፋስ
ይህ ጥቂቱን የወንዞች ውሃ የሚያደርቅ ሞቃት ነፋስ ነው፡፡
# ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ
‹‹ሰዎች ጫማቸውን እንዳደረጉ እንዲሻገሩት››