am_tn/ezk/45/06.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል፣ ለእስራኤል ቤት ያለውን መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አምስት ሺህ ክንድ… ሃያ አምስት ሺህ

እያንዳንዱ ረጀም ክንድ ወደ 54 ሴንቲ ሜትር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 40፡5 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "5000 ክንድ … 25000 ክንድ" ወይም "ወደ 2.7 ኪሎ ሜትር …ወደ 13.5 ኪሎ ሜትር" (መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የርቀት መለኪያ የነበሩ የሚለውን ይመልከቱ)

ለቅዱስ ስፍራ የተጠበቀ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንተ ለቅዱስ ስፍራ የሰጠኸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁመቱ ከእነዚያ ክፍሎች/ድርሻ ቁመት ጋር ይመጣጠናል

ሕዝቅኤል የልዑላኑን መሬት ለእያንዳንዱ ነገድ ከተሰጠው መሬት መጠን ጋር እንደሚያነጻጽር በውስጠ ታዋቂነት ተጠቁሟል፡፡ "ቁመቱ ለነገዶቹ ከተሰጠው ድርሻ ቁመት ጋር ተመሳሳይ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከምዕራብ እስከ ምስራቅ

እነዚህ የእስራኤል ምዕራባዊ እና ምስራቃዊ ድንበሮች መሆናቸው በውስጠ ታዋቂነት ተጠቁሟል፡፡ "በባህሩ ከሚገኘው ከእስራኤል ምዕራባዊ ዳርቻ በዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚገኘው ምስራቃዊ ዳርቻ"