1.9 KiB
1.9 KiB
አጠቃላይ መረጃ፡
ያህዌ ዳግም የኢየሩሳሌም እና የሰማርያ ከተሞችን ሁለት ዘማዊያን እንደሆኑ አድርጎ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
መልዕክተኛ ወደሚላክላቸው፣ ከሩቅ አገር ለሚመጡ ወንዶች መልዕክተኛ ላክሽ
እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ይህ ማለት ወደ እነርሱ እንዲመጡ ሩቅ አገር ወዳሉ ወንዶች መልዕክተኛ ላኩ፡፡ "ከሩቅ ስፍራ ወደሚመጡ ወንዶች መልዕክተኞች ላክሽ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
እነሆ!
"ተመልከቱ" ወይም "አድምጡ" ወይም "ቀጥሎ ለምነገረራችሁ ትኩረት ስጡ"
ገላሽን ታጠብሽ፣ ዐይንሽን ተኳልሽ፣ ደግሞም ራስሽን በጌጣጌጥ አስዋብሽ
እነዚህ ነገሮች አንዲት ሴት ራሷን ለአንድ ወንድ ይበልጥ ውብ ሆና ለማሳየት የምታደርጋቸው ነገሮች ናቸው፡፡
አንቺ ገላሽን ታጠብሽ…ተቀመጥሽ
እዚህ ስፍራ "አንቺ" የሚለው ቃል ወደ ነጠላ ቁጥር ይለወጣል፣ እናም አንደኛይቱን እህት ያመለክታል፣ ነገር ግን ሁኔታው ምናልባት ለሁለቱም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡ በእናንተ ቋንቋ ሀሳቡን ለመግለጽ አንዲቱ እህት መለየት የሚኖርባት ከሆነ ኦሖሊባ መሆኗን ጥቀሱ፡፡ (አንተ/አንቺ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይምልከቱ)
ቅመሜ እና ዘይቴ
እነዚህ ነገሮች ያህዌን ለማምለክ የሚያገለግሉ ነገሮች ናቸው፡፡