1.8 KiB
1.8 KiB
አጠቃላይ መረጃ፡
ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እርሷ የእኔ በነበረች ጊዜ
ይህ የሚያመለክተው እርሷ መቼ የእርሱ ሚስት እንደነበረች ነው፡፡ "እርሷ የእኔ ሚስት እስከ ነበረች ጊዜ ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
በላያቸው የነበሩ
"ይገዟቸው የነበሩ"
የአሶር ምርጥ ወንዶች የነበሩ ሁሉ
ይህ የሚገልጸው "እነርሱ" የሚለው ቃል ማንን እንደሚያመለክት ነው፡፡
አብራቸው ካመነዘረቻቸው እና ከጣኦቶቻቸው ጋር ሁሉ ረክሳለች
ይህ የሚያመለክተው ከእነዚህ ሁሉ ወንዶች ጋር መተኛቷን እና ጣኦቶቻቸውን ማምለኳን ነው፡፡ "ከሁሉም ጋር በመተኛት እና ጣኦቶቻቸውን በማምለክ ራሷን አርክሳለች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
መርከስ/ንጹህ አለመሆን
እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ነገር ንጹህ አድርጎ የማይቆጥረው ወይም የረከሰ ሰው በአካል እንደቆሸሸ ተደርጎ ይገለጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)