am_tn/ezk/23/01.md

3.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በዘይቤ ኢየሩሳሌምን እና ሰማርያ ከተሞችን ለእርሱ እንዴት ታማኝ እንዳልሆኑ እንደ ሁለት ዘማዊያት እህትማማቾች አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን አንዳች ነገር ለማስተዋወቅ ያገለገለ ፈሊጥ ነው ፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላቶች ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ይህን ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው እንጂ ሌላ አለመሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰብአዊ ፍጡር ግን እንዲያ አይደለም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ጡቶቻቸው ተዳበሰዋል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወንዶች ጡቶቻቸውን ዳበሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የድንግልና ጡቶቻቸው አጎጠጎጤአቸው ተዳብሷል

ይህ ሀረግ ከመጀመሪያው ሀረግ ጋር በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አለው፤ ትኩረት የሚሰጠውም የሁለቱን ወጣት ሴቶች ስነምግባር የጎደለው ባህርይ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወንዶቻቸው የድንግልና ጡቶቻቸውን አጎጠጎጤ ዳበሱ" (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

መዳበስ

በፍቅር ወይም በልስላሴ መነካት

እነርሱ የእኔ ሆኑ

ይህ ማለት እርሱ አገባቸው ደግሞም ሚስቶቹ ሆኑ፡፡ "እነርሱ የእኔ ሚስቶች ሆኑ" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የስሞቻቸው ትርጉም ይህ ነው፡ ኦሖላ ማለት ሰማርያ ማለት ሲሆን፤ ኦሖሊባ ማለት ኢየሩሳሌም ናት፡፡

"ኦሖላ ሰማርያን ትወክላለች፤ ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌምን ትወክላለች፡፡" በዚህ ዘይቤ ሰማርያ የተገለጸችው ኦሖላ እንደሆነች እና ኢየሩሳሌም ደግሞ ኦሖሊባ እንደሆነች ተደርጎ ነው፡፡ ይህ የመሚገልጸው እነዚህ ከተሞች ታማኝ እንዳልሆኑ ሚስቶች እንዴት ለያህዌ ታማኞች እንዳልነበሩ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኦሖላ

ይህ የሴት ስም ሲሆን ትርጉሙ "የእርሷ ድንኳን" ማለት ነው ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ኦሖሊባ

ይህ የሴት ስም ሲሆን ትርጉሙ "የእኔ ድንኳን በእርሷ ነው" (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)