am_tn/ezk/20/45.md

2.4 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ፊትህን ወደ ደቡቡ ምድር አቅና

ይህ በዚያ የሚኖረውን ሕዝብ የመቅጣት ምልክት ይሆን ዘንድ በደቡቡ ምድር ላይ እንዲያፈጥ የተሰጠ ትዕዛዝ ነው። ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 4፡3 ላይ እንድት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በደቡቡ ምድር ላይ አፍጥጥ” ወይም “ጉዳት ይደርስባቸው ዘንድ በደቡቡ ምድር ላይ አፍጥጥ” (See: Symbolic Action)

ፊትህን አቅና

እዚህ ጋ “ፊት” ትኩረት የመስጠት ወይም የማፍጠጥ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ፊትህ አቅና” ማፍጠጥን ይወክላል። አ.ት፡ “አፍጥጥ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሚንበለበለውን እሳት አያጠፉትም

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚንበለበለው እሳት አይጠፋም” ወይም “የሚንበለበለውን እሳት ማንም ሊያጠፋው አይችልም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለው ፊት ሁሉ ይቃጠላል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እሳቱ ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት ሁሉ ያቃጥላል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለው ፊት ሁሉ

እዚህ ጋ “ፊት” የሚለው ቃል ሰውዬውን ይወክላል። እግዚአብሔር ተቃራኒዎቹን አቅጣጫዎች በመጥቀሱ በሰሜንና በደቡብ የሚኖሩትን ሁሉ እንዲሁም በመካከል የሚኖሩትን ሁሉ ያመለክታል።