20 lines
1.3 KiB
Markdown
20 lines
1.3 KiB
Markdown
# ለመማል እጄን አንሥቻለሁ
|
|
|
|
እዚህ ጋ “እጄን አንሥቻለሁ” የሚለው አባባል ለማድረግ የማለውን ነገር በእርግጠኝነት እንደሚያደርገው የሚያሳይ ምልክታዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “በጽኑ መሐላ ምያለሁ” (See: Symbolic Action)
|
|
|
|
# ትዝ ይላችኋል
|
|
|
|
የዚህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም ማስታወስ ማለት ነው። አ.ት፡ “ታስታውሳላችሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
|
|
|
|
# ራሳችሁን አርክሳችኋል
|
|
|
|
ለእግዚአብሔር ዓላማ ተቀባይነትን ያላገኘ ያ ሰው እንደ ረከሰ ተቆጥሮ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
|
|
|
# በዐይኖቻችሁ ፊት ራሳችሁን ትንቃላችሁ
|
|
|
|
እዚህ ጋ ዐይን ማየትን፣ ማየትም አሳብን ወይም ውሳኔን ይወክላል። አ.ት፡ “ራሳችሁን ትጠላላችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
|
|
|
# ስለ ስሜ ስል
|
|
|
|
እዚህ ጋ “ስም” የሚለው ቃል የሚወክለው የእግዚአብሔርን ዝና ነው። አ.ት፡ “በዝናዬ ምክንያት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|