am_tn/ezk/20/30.md

2.5 KiB

በአባቶቻችሁ መንገድ ራሳችሁን የምታረክሱት ለምንድነው?

እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመገሰጽ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “አባቶቻችሁ ያደረጓቸውን ነገሮች በማድረግ ራሳችሁን ማርከስ የለባችሁም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ራሳችሁን የምታረክሱት ለምንድነው

ለእግዚአብሔር ዓላማ ተቀባይነት የሌለው ያ ሰው በአካሉ ጭምር እንደ ረከሰ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አስከፊ ነገሮችን በመፈለግ እንደ ዝሙት አዳሪ የምታደርጉት ለምንድነው?

እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመገሰጽ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “አስከፊ ነገሮችን እንደምትፈልግ ዝሙት አዳሪ ልታደርጉ አይገባችሁም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እንደ ዝሙት አዳሪ የምታደርጉት ለምንድነው

ካላገቧት ወንዶች ጋር እንደምትተኛ ሴት ሕዝቡ ታማኝ ስላለመሆኑ እግዚአብሔር ይናገራል። (See: Simile)

ወንዶች ልጆቻችሁ በእሳት እንዲያልፉ በምታደርጉበት ጊዜ

“ወንዶች ልጆቻችሁን እሳት ውስጥ በምትጨምሩበት ጊዜ”። የሚቃጠል ቁርባን አድርገው ወንዶች ልጆቻቸውን እሳት ውስጥ ይጨምሩ እንደነበር ግልጽ አይደለም። ይህ ሐረግ ስጦታቸውን እንዴት አድርገው ይሠዉ እንደ ነበረ ያብራራል

የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ታዲያ ትፈልጉኝ ዘንድ ለምን እፈቅድላችኋለሁ?

እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመገሰጽ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እንድትቀርቡኝ አልፈቅድላችሁም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ሕያው እንደ መሆኔ

እግዚአብሔር ቀጥሎ የሚናገረው የተረጋገጠ እውነት መሆኑን ለማሳየት ይህንን አገላለጽ ይጠቀማል። ይህ ጽኑ ተስፋ የመስጫ መንገድ ነው። አ.ት፡ “ጽኑ መሐላ አደርጋለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)