2.2 KiB
በሥርዓቶቼ አልሄዱም
ሥርዓቶቹ አንድ ሰው የሚራመድባቸው መንገዶች የሆኑ ይመስል እግዚአብሔር ሥርዓቶቹን ስለሚታዘዝ ሰው ይናገራል። አ.ት፡ “ሥርዓቶቼን አልታዘዙም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ንዴቴን በእነርሱ ላይ ለማፍሰስ
ንዴቱ በእነርሱ ላይ የሚያፈሰው ፈሳሽ የሆነ ይመስል እግዚአብሔር እነርሱን በመቅጣት ንዴቱን እንደሚገልጽ ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 20፡8 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በእነርሱ ላይ ንዴቴን አሳያለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እጄን አራቅሁ
እዚህ ጋ “እጅ” የሚለው ቃል የሚወክለው እግዚአብሔርን ሲሆን እጁን ማራቅ ማለት ሊያደርግ የነበረውን አላደረገም ማለት ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን ያንን አላደረግሁም” (Synecdoche እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ስለ ስሜ ስል
እዚህ ጋ “ስም” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ዝና ይወክላል። አ.ት፡ “ስለ ዝናዬ ስል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በሀገራቱ ዐይን ፊት እንዳይሰደብ
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በሕዝቅኤል 20፡9 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በሀገራቱ ዐይን ፊት ሰዎች እንዳይሰድቡት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
በሀገራቱ ዐይን ፊት
እዚህ ጋ “ሀገሮች” የሚያመለክተው በእነዚያ ቦታዎች የሚኖሩትን ሕዝቦች ነው። ዐይኖች ማየትን፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላሉ። አ.ት፡ “በሌሎች ሀገሮች በሚኖሩ ሰዎች አስተሳሰብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)