am_tn/ezk/20/04.md

2.2 KiB

ትፈርድባቸዋለህ? የሰው ልጅ ሆይ፣ ትፈርዳለህ?

ሕዝቅኤል ፍርድን ለማስታወቅ ያለውን መሰጠት እንዲጠብቀው እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን አንዱን ጥያቄ ሁለት ጊዜ ይጠይቀዋል። አ.ት፡ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነርሱ ላይ ፍርድን ለማስታወቅ ዝግጁ ነህ?”

እኔ . . . መሐላ ለመማል እጄን እንሥቻለሁ

እዚህ ጋ “እጄን አንሥቻለሁ” የሚለው ሐረግ ለማድረግ የማለውን ቃል ያለ ጥርጥር እንደሚያደርገው የሚያሳይ ምልክታዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “እኔ . . . ጽኑ መሐላ ምያለሁ”

የያዕቆብ ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮችን ያመለክታል። “የ-- ቤት” የሚለውን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዳለው አድርገህ ተርጉመው። አ.ት፡ “የያዕቆብ ዘር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ወተትና ማር የምታፈስ

“ብዙ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር ነበረች”። ወተቱና ማሩ ከእነዚያ እንስሳትና እጽዋት በምድሪቱ ላይ የሚፈስ በሚመስልበት መልኩ ምድሪቱ ለእንስሳትና ለእጽዋት ጥሩ መሆኗን እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ከብት ለማርባትና እህል ለማብቀል ምድሪቱ እጅግ በጣም ጥሩ ነበረች” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በምድሪቱ መካከል ሁሉ እጅግ ያማሩ ጌጣ ጌጦች

ሰዎች የሚኖሩባት ምድር ጌጣ ጌጦች ወይም ሌላ ለማየት የሚያስደስቱ ነገሮችን በሚመስሉበት ሁኔታ ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “ከምድር ሁሉ እጅግ ያማረች” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)