am_tn/ezk/17/09.md

28 lines
2.5 KiB
Markdown

# ይሳካለት ይሆን?
አሉታዊው ምላሽ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ዋነኛ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አይሳካለትም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
# እንዲጠወልግና ቀንበጡ ሁሉ እንዲደርቅ ከሥሩ አይነቀለም? ፍሬውስ አይረግፍም?
በወይኑ ተክል ላይ በእርግጠኝነት እንደሚፈረድበት አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። ጥያቄው እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል፤ ደግሞም በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ሥሮቹን ይነቅላል፣ የቅጠሎቹ ዕድገት በሙሉ እንዲጠወልግም ፍሬዎቹን ይቀጥፋል፝” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
# እርሱን ለመንቀል ብርቱ ክንድ ወይም ብዙ ሰዎች አያስፈልጉም
“ብርቱ ክንድ” የሚለው ሐረግ ብርቱ ሰውን ይወክላል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እርሱን ለመንቀል ብርቱ ሰው ወይም ብዙ ሰዎች አያስፈልጉም” (Synecdoche እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
# እነሆ
“ተመልከቱ” ወይም “ስሙ” ወይም “የምነግራችሁን ልብ በሉ”
# ያድግ ይሆን?
አሉታዊው ምላሽ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ዋነኛ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አያድግም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
# የምስራቅ ንፋስ በሚነካው ጊዜ እርሱ አይጠወልግም?
ይህ በእርግጥ እንደሚሆን አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይቻላል። አ.ት፡ “የምስራቅ ንፋስ በሚነካው ጊዜ ይጠወልጋል”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
# የምስራቅ ንፋስ በሚነካው ጊዜ
“የምስራቅ ንፋስ በሚነፍስበት ጊዜ”