1.3 KiB
1.3 KiB
ልብ በይ
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉሙ ማስታወስ ማለት ነው። አ.ት፡ “አስታውሽ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በቁጣ እንድንቀጠቀጥ አድርገሽኛል
እዚህ ጋ “መንቀጥቀጥ” የሚያመለክተው አንድ ሰው እጅግ በሚቆጣበት ጊዜ የሚታይበትን አካላዊ ምላሽ ያመለክታል። ኢየሩሳሌም እነዚህን ነገሮች ስታደርግ ልጅ በነበረችበት ጊዜ እግዚአብሔር ያደረገውን አላሰበችም።
እነሆ
እዚህ ጋ፣ “እነሆ” የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው አስገራሚ መረጃ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል።
ስላደረግሽው ነገር እኔ ራሴ ቅጣቱን በራስሽ ላይ አመጣለሁ
“በራስሽ ላይ አመጣለሁ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ይህንን ቅጣት ትቀበላለች ማለት ነው። ይህንን የአነጋገር ዘይቤ በሕዝቅኤል 11፡21 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ስለ ጸባይሽ በምትቀበይው ቅጣት እንድትሰቃዪ አደርግሻለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)