2.0 KiB
2.0 KiB
ለእኔ የወለድሻቸውን
“ልጆቼ የነበሩትን”
እንደ ምግብ እንዲበሏቸው ለምስሎቹ ሰዋሻቸው … በእሳት እንዲያልፉ አደርግሻቸው
እዚህ ጋ፣ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ ስላደረጉት አንድ ነገር ይናገራል። ልጆቻቸውን ለአሕዛብ ጣዖታት ሰውተዋል።
እንደ ምግብ እንዲበሏቸው ለምስሎቹ ሰዋሻቸው
በእነዚህ ጥንታዊ የጣዖት አምላኪዎች መስዋዕት አማልክቱ የሚቀርብላቸውን ምግብ እንደሚበሉ ሰዎች ያምኑ ነበር። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ምስሎቹ እንደ ምግብ እንዲበሏቸው ለእነዚያ ምስሎች መስዋዕት አደረግሻቸው”
የአመንዝራነትሽ ሥራ አነስተኛ ጉዳይ ነው? አረድሻቸው
ሴቲቱ አመንዝራነቷ ሳያንሳት ልጆቿን ደግሞ ለመሰዋት መወሰኗ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ያረድሻቸው የአመንዝራነትሽ ሥራ አነስተኛ ጉዳይ እንደ ሆነ ስላሰብሽ መሆን አለበት” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
በእሳት እንዲያልፉ አደርግሻቸው
ለምስሎቿ የሚቃጠል መስዋዕት እንዲሆኑ እሳት ውስጥ እንደጨመረቻቸው ግልጽ አይደለም። አ.ት፡ “የሚቃጠል መስዋዕት አድርጋ ሰዋቻቸው”
ዕርቃንሽን እና ራቁትሽን
የእነዚህ የሁለቱም ቃላት ትርጉም አንድ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 16፡7 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ባዶ ዕርቃን”