am_tn/ezk/06/01.md

3.1 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንዳች ነገር መናገሩን ለማስታወቅ ጥቅም ላይ የዋለ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እግዚአብሔር እነዚህን ቃላት ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

ፊትህን በእስራኤል ተራሮች ላይ አንሣ

ይህ በዚያ ያሉትን ሰዎች ስለ መቅጣቱ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በተራሮቹ ላይ እንዲያፈጥ የተሰጠ ትዕዛዝ ነው። ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 4፡3 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በእስራኤል ተራሮች ላይ አፍጥጥ” ወይም “በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ጉዳት ያገኛቸው ዘንድ በእስራኤል ተራሮች ላይ አፍጥጥ”

ፊትህን በእስራኤል ተራሮች ላይ አቅና

ፊትህን በእስራኤል ተራሮች ላይ አቅና የእስራኤል ተራሮች የሚገኙት ርቀት ላይ ነበር፤ በመሆኑም ሕዝቅኤል ሊያያቸው አይችልም፤ ነገር ግን በዚያ አቅጣጫ ማፍጠጡ የመጎዳታቸው ምልክት ነበር። አ.ት፡ “ወደ እስራኤል ተራሮች ዙርና አፍጥጥባቸው” ወይም “በዚያ ያሉ ሰዎች ጉዳት እንዲደርስባቸው በእስራኤል ተራሮች አቅጣጫ አፍጥጥ”

ፊትህን አቅና

እዚህ ጋ “ፊት” የትኩረት ወይም የመመልከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ተራሮች

“በእስራኤል ምድር ያሉ ተራሮች”

እነሆ!

“ተመልከቱ!” ወይም “ስሙ!” ወይም “የምነግራችሁን ልብ በሉ!”

ጌታ እግዚአብሔር

ይህንን በሕዝቅኤል 2:4 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

ሰይፍን አመጣባችኋለሁ

“ሰይፍ” የሚለው ቃል ሰይፍን በመጠቀም ሰዎችን የሚገድሉትን ወታደሮች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ወታደሮች መጥተው እንዲገድሏችሁ እጠራቸዋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)