am_tn/mat/10/37.md

3.8 KiB

ማቴዎስ 10፡37-39

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ስደት መፍራት የሌለባቸው በምን ምክንያት እንደሆነ ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ የሚወድ . . . ሊሆን አይገባውም፤ ኤቲ፡ “የሚወድ . . . ሊሆን አይገባውም፤” ወይም “የሚትወዱ ከሆነ . . . አትገቡም” የ ይህ “ማንም” ወይም “ይህንን የሚያደረግ” ወይም “ይህንን የሚያደረግ ማንን ሰው” ወይም “ይህንን የሚያደርጉ ሰዎች” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ መውደድ በዚህ ሥፍራ ላይ መውደድ የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው “ወንድማዊ መዋደድን” ወይም “ከጓደኛ የሚገኝ ፍቅርን” የሚያመለክት ነው፡፡ በተጨማሪም “መንከባከብ” ወይም “መሰጠት” ወይም “የሚገኝ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ይህ እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “የእኔ ሊሆን ፈጽሞ አይገባውም” ወይም “የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይገባውም” ወይም “የእኔ መሆን አይገባውም” የማይዝ . . . አይሆንም አማራጭ ትርጉሞች፡ “የማይዙ . . አይደሉም” ወይም “የማትይዝ ከሆነ . . . አይደለህም” ወይም “የማትይዙ ከሆነ . . . አይደላችሁም፡፡” አንሣ . . . መስቀሉን እና ተከተለኝ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ለመሞት ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው፡፡ ማንሣትን እና ከሌላ ሰው ኋላ መከተልን የሚያመለክቱ የተለመዱ ቃላትን ተጠቀም፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) አንሣ “አንሣ” ወይም “አንሣና ተሸከም” የሚያገኝ . . . ያጠፋታል . . የሚያጠፋ . . . ያገኛታል፡፡ እነዚህ ቃላት በተቻለ መጠን በጣም ትንሽ ቃላት አማካኝነት ሊተረጎሙ ይገባል፡፡ አማራጨ ትርጓሜዎች፡ “የሚያገኗት. . . ያጠፏታል . . . የሚያጠፏት . . . ያገኟታል” ወይም “ካገኘሃት . . . ታጠፋታለህ . . . ካጠፋሃት . . . ታገኛታለህ” ማግኘት ይህ “መጠበቅ” ወይም “ደንነቱን መጠበቅ” ከሚለው ቃል ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ያለው ነው፡፡ አማራጭ ትርጓሜዎቹ፡ “ለመጠበቅ የሚሞክር” ወይም “ለማዳን የሚሞክር” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] ተመልከት) ያጠፋታል ይህ ሰውዬው ይሞታል ማለት አይደለም፡፡ “እውነተኛ ሕይወት አይኖረውም” ለሚለው ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) ነፍሱን የሚያጠፋ ይህ ማለት መሞት ማለት አይደለም፡፡ ይህ ማለት ከራሱ ሕይወት ይልቅ ኢየሱስን መታዘዝ አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “የራሱን ሕይወት የካደ፡፡” ለእኔ ሲል “በእኔ በማመኑ ምክንያት” ወይም “ለእኔ ሲል” ወይም “በእኔ ምክንያት”፡፡ ይህ በ MAT 10:18. ላይ ካለው “ለእኔ ሲል” ከሚለው ሀረግ ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ያለው ነው፡፡ ያገኛታል ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ትርጉሙ “እውነተኛ ሕይወትን ያገኛል” ማለት ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት)