1.2 KiB
1.2 KiB
ያህዌ በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱን ማግኘት በሚቻልበት ጊዜ ያህዌን ፈልጉት››
ክፉ መንገዱን ይተው
‹‹ክፉ›› የሚያመለክተው ክፉ ሰውን ነው፡፡ ከዚህ በፊት ይራመዱበት በነበረው መንገድ መራመድ እንደ ተወ ሰው፣ ክፉ ሰዎችም ከእንግዲህ ኀጢአት እንደማያደርጉ ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉዎች አኗኗራቸውን ይለውጡ››
በደለኛም ሐሳቡን
ግሡ ካለፈው ሐረግ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀጢአተኛ ሰው ሐሳቡን ይተው››
ሐሳቡን
ይህም ማለት፣ 1) ‹‹አስተሳሰቡን›› ወይም 2) ‹‹ዕቅዱን››
ያዝንለታል
‹‹ያህዌ ያዝንለታል››
ወደ አምላካችን
ግሡ በዚህ ዐረፍተ ነገር የመጀመሪያ ሐረግ ውስጥ ይገኛል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ አምላካችን ይመለስ››