32 lines
1.9 KiB
Markdown
32 lines
1.9 KiB
Markdown
# አጠቃላይ መረጃ
|
|
|
|
ኢሳይያስ ስለ ያህዌ ባርያ መናገር ቀጥሏል (ኢሳይያስ 53፥1-2 ይመ.)
|
|
|
|
# ዘሩን ያያል
|
|
|
|
እዚህ ላይ፣ ‹‹ዘሩ›› ማለት ከባርያው መሥዋዕት የተነሣ ያህዌ ይቅር ያላቸውን ሰዎች ነው፡፡
|
|
|
|
# ዕድሜውም ይረዝማል
|
|
|
|
ይህ የሚናገረው ብዙ ዘመን እንደሚኖር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ባርያውን እንደ ገና እንዲኖር ያደርጋል››
|
|
|
|
# የያህዌ ዓላማ በእርሱ ይከናውናል
|
|
|
|
ይህን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ በባርያው በኩል ዓላማውን ያከናውናል››
|
|
|
|
# ከሕይወቱ ስቃይ በኃላ
|
|
|
|
‹‹ሕይወቱ›› የሚለው የሚያመለክተው የያህዌን ባርያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የያህዌ ባርያ መከራ ከተቀበለ በኃላ››
|
|
|
|
# ብርሃን ያያል
|
|
|
|
እዚህ ላይ፣ ‹‹ብርሃን›› የሚለው ሕይወትን እንደሆነ ብዙ ቅጂዎች ይገነዘባሉ፡፡ ይህም ባርያው እንደ ገና ይኖራል ማለት ነው፡፡
|
|
|
|
# ጻድቅ ባርያዬ
|
|
|
|
እዚህ ላይ፣ ‹‹የእኔ›› የሚለው ያህዌ ነው፡፡
|
|
|
|
# ርኩሰታቸውን ይሸከማል
|
|
|
|
‹‹ይሸከማል›› ማለት፣ ይወስዳል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ርኩሰታቸው›› የኀጢአታቸውን ቅጣት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቅጣታቸውን ይወሰድዳል›› ወይም፣ ‹‹ለኀጠአታቸው ይቀጣል›› ወይም 2) ‹‹ርኩሰታቸው›› በደልን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በደላቸውን በራሱ ይወስዳል›› ወይም፣ ‹‹ለኀጢአታቸው በደለኛ ይሆናል፡፡››
|