am_tn/isa/33/03.md

1.7 KiB

ከከፍተኛ ድምጽ የተነሣ ሰዎች ሸሹ

ከፍተኛ ድምጽ የሚለውን በሚመለከት ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) የእግዚአብሔርን ድምጽ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ከአንተ ከፍተኛ ድምጽ የተነሣ ሰዎች ሸሹ' ወይም 2) የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከፍተኛ ድምጽ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ከሠራዊትህ ድምጽ የተነሣ ሰዎች ሸሹ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ተነሥ

ይህ አንድ ነገር ለማድረግ መጀመር ማለት ነው፡፡ አት፡- "መሥራት ጀምር' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

አሕዛብ ተበተኑ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "አሕዛብን በተንክ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

አንበጦች እንደሚሰበሰቡ ምርኮህ ይሰበሰባል፣ አንበጦች እንደሚዘልሉ ሰዎች ይዘልሉበታል

ይህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጠላቶቻቸው ምርኮ በማረኩ ጊዜ የሚያሳዩትን ከፍተኛ ፍጥነትና ጉጉት ምግብ በሰበሰቡ ጊዜ ከሚታየው የአንበጦች መጓጓት ጋር ያስተያያል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "አንበጦች አረንጓዴ ተክልን እንደሚበሉ በተመሣሣይ መስገብገብ ሕዝብህ ከጠላቶችህ ምርኮ ይሰበስባሉ' (ዘይቤአዊ ንግግርና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)