28 lines
1.9 KiB
Markdown
28 lines
1.9 KiB
Markdown
# ከእግዚአብሔር ደምጽ የተነሳ አሦር ይሰባበራል
|
|
|
|
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር በመናገር የአሦርን ወታደሮች ይሰባብራቸዋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
|
|
|
|
# አሦር ይሰባበራል
|
|
|
|
አሦር የእግዚአብሔር ድምጽ የሚሰባብረው እቃ እንደሆነ አድርጎ ኢሳይያስ ስለ አሦር ፍርሃት ይናገራል፡፡ አት፡- "አሦር ይደነግጣል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
|
|
|
|
# አሦር
|
|
|
|
በዚህ ስፍራ የአሦርን ወታደሮች ይወክላል፡፡
|
|
|
|
# እግዚአብሔር በላዩ የሚያወርድበት የተመደበበት በትር ሁሉ
|
|
|
|
እግዚአብሔር ሠራዊቱ አሦራውያንን እንዲያሸነፉ ማድረጉ እግዚአብሔር አሦራውያንን በበትር እንደሚመታ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
|
|
|
|
# ይታጀባል
|
|
|
|
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የይሁዳ ሰዎች አብረውት ይሆናሉ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
|
|
|
|
# ከበሮ
|
|
|
|
ሊመታ የሚችል ታምቡር የሚመስል ከላዩ ያለውና ሲነቃነቅ ድምጽ የሚሰጡ የብረት ቁርጥራጮች ዙሪያውን ያሉት የሙዚቃ መሣሪያ ነው፡፡ ይህንን በኢሳይያስ 5፡12 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
|
|
|
|
# ከእነርሱ ጋር ይዋጋል
|
|
|
|
እግዚአብሔር ሠራዊቱ አሦራውያንን እንዲያሸነፉ ማድረጉ እግዚአብሔር ከጠላት ሠራዊት ጋር የሚዋጋ ተዋጊ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
|