am_tn/isa/27/09.md

2.1 KiB

ስለዚህ እንዲሁ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) እንዲሁ የሚለው ኢሳይያስ በቀደመው ጥቅስ እንደገለጸው እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ ምርኮ መሰደዱን ያመለክታል ወይም 2) እንዲሁ የሚለው ኢሳይያስ በቁጥር 9 ቀጥይ ክፍል የሚገልጻቸውን ድርጊቶች ያመለክታል፡፡

የያዕቆብ በደል ይሰረያልና

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ከእስራኤል ኃጢአትን ያስወግዳል' ወይም "እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን ኃጢአት ይቅር ይላል፡፡' (አድጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የያዕቆብ በደል … የእርሱን ኃጢአት የማስወገድ

በዚህ ስፍራ "ያዕቆብ' የያዕቆብን ልጆች ይወክላል፡፡ አት፡- "የእስራኤላውያን በደል… የእነርሱን ኃጢአት የማስወገድ' (ምትክ ስም ተመልከት)

ይህም

በዚህ ስፍራ "ይህ' በቁጥር 9 ቀጥይ ክፍል ኢሳይያስ የሚገልጻቸውን ድርጊቶች ያመለክታል፡፡

ሙሉ ፍሬው

ፍሬ በዛፍ ላይ ወይም በወይን ተክል ላይ እንደሚያድግ ይህ የድርጊቱን ውጤቶች ይናገራል፡፡ አት፡- "ውጤቱ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የመሠዊያ ድንጋዮችን እንደ ኖራ ድንጋይ ያደርጋቸዋል ያደቅቃቸዋልም፣ የአሼራህ ዐፀዶች ወይም የማጠኛ መሠዊያዎች ጸንተው አይቆሙም

በዚህ ስፍራ እርሱ የሚለው ልጆቹን የሚወክለውን ያዕቆብን ያመለክታል፡፡ አት፡- "ለሐሰተኛ አማልክት የሚሠውባቸውን መሠዊያዎች ፈጽመው ያፈርሳሉ፣ የአሼራህን ጣዖታትና ለሐሰተኛ አማልክት እጣን የሚያቃጥሉባቸውን መሠዊያዎች ሁሉ ያስወግዳሉ፡፡' (ምትክ ስም ተመልከት)