am_tn/isa/09/03.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ የሚያድነው መቼ እንደሆነ መናገር ቀጥሏል፡፡ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት ወደ ፊት ቢሆንም (ኢሳይያስ 9፥1) ኢሳይያስ አሁን እንደ ተፈጸሙ አድርጐ ይናገራል፡፡ ይህም በትክክል እንደሚፈጸሙ አጽንዖት ይሰጣል፡፡

ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ

‹‹አንተ›› የሚለው የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ ‹‹እነርሱ›› የሚለው የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፤ እንደ እስራኤል አካል ኢሳይያስ ራሱንም ይጨምራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ አንተ ሕዝባችንና ደስታችንን እጅግ ታበዛለህ››

ሰዎች ምርት ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል፡፡

ያህዌ ለእስራኤል የሚሰጠው ደስታ ምርት ሲሰበስቡና ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሰዎች ዐይነት ደስታ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ምርት ሲሰበስቡ፣ ጦርነት ካበቃ በኃላ ወታደሮቹ የወሰዱትን ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል››